Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

EPRDF
Member
Posts: 2162
Joined: 26 Jan 2010, 12:58

Re: አጼ ምኒልክ እና የኢትዮጵያ ሙስሊሞች (ባላገሩ ቲቪ)

Post by EPRDF » 26 May 2020, 20:11

ዋጆ ሆረስ፣

ለትሬድህ አፄ ምኒልክና የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ብለህ አርዕስት የሰጠሀው ግን ለምንድነው?

ምኒልክ ቤተመንግስቱን ሊያሰራው ከውጭ ሐገር ላስመጣው አንድ የሕንድ ሙስልም የመስገጃ ቦታ መኖርያ ቤቱ ሰፈር ዉስጥ ስለፈቀደለት፣ ለኢትዮጵያ ሙስልሞች ምኒልክ መልአክ ነበር ለማለት ነው ዳር ዳር የምትለው ወይስ እንዴት ነዉ ኣልገባንም።

በምኒልክና በተለይም ይህ ቪዲዮ ላይ ስሙ የተጠቀሰው የጦር ሚንስትሩ በሃብተጊዮርጊስ ድንጉዴ ዘመን ፣ ለኢትዮጵያ ሙስልሞች የመጨረሻው አስከፊና ጨለማ ዘመን እንደነበር በታሪክ ተመዝግቦዋል።

"የመጀመሪያው የአዲስ አበባ መስጂድ በሚኒልክ ዘመን" ከሚል አርዕስት ጋር ብትመጣና የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የሚለውን ቃል ባታካትት ጥሩ ነበር ፣ ምክኒያቱም.....

የተጓዘው ሽሕር ለልደት ባይደርስ
እሱ ላም አርዶ ዋለ የሽዋው ንጉስ
(እስላም)

የተባለለት ዘመን ነበር ዘመኑ ለማለት ነው አመሰግናለሁ።

Horus
Senior Member+
Posts: 40193
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አጼ ምኒልክ እና የኢትዮጵያ ሙስሊሞች (ባላገሩ ቲቪ)

Post by Horus » 26 May 2020, 23:52

EPRDF,

አንተ ብሎ ጸረ ምኒልክ?! እስቲ አንድ ቦታ ምኒልክ ሙስሊሞችን ሲያጠቃ በታሪክ ጥቀስ? ነገር ግን ግራኝ መሃመድ የኢትዮጵያን የስንት መቶ አመታት ስልጣኔ በእሳት ስላጋየና ስንት ሺ የክርስቲያ ደም በግፍ ካፈሰሰ በኋላ በሁለቱ እምነቶች መሃል ይህን ሁሉ ታሪካዊ ሰላምዊ አብሮ መኖርና ወዳጅነት መኖሩ የኢትዮዊያንና ገዝዎችዋ ትልቅነት ማሳያ ነው ። ሌላው የሙስሊሙ አለም ሺአ ሱኒ ተባብሎ ሲተራረድ ። ፈጣሪ እንደንተ ካለ ህመምተኛ ህዝባችንን ይጠብቅ !

EPRDF
Member
Posts: 2162
Joined: 26 Jan 2010, 12:58

Re: አጼ ምኒልክ እና የኢትዮጵያ ሙስሊሞች (ባላገሩ ቲቪ)

Post by EPRDF » 28 May 2020, 00:28

Horus wrote:
26 May 2020, 23:52
EPRDF,
ፈጣሪ እንደንተ ካለ ህመምተኛ ህዝባችንን ይጠብቅ !
እንዴ ዋጆ ሖረስ! አንተ ራሥህ ያመጣሀው ቪዲዮ የሚተርከው ነው እንግዲህ፣ ምኒልክ ለምሕንድስና ላመጣው የውጭ ዜጋ ትንሽ ጎጆ እንዲሰግድበት የፈቀደለት እንጂ ለራሱ የሙስሊም ዜጎች ምኒልክ ኣዝኖ የፈቀደው የስግደት ጎጆ ኣይደለም። አንተ ምኒልክና የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ብለህ በማወናበድ ምኒሊክ ለሙስሊም ዜጎች እምነታቸውን እንዲያከብሩበት የለገሳቸው ቦታ እንደሆነ ልታሳምነን እይተቃጣህ እኮ ነው፣ እኔ ደግሞ አይደለም ተው አትቅጠፍ እያልኩህ ነው እና ይህ ታድያ ምኑ ላይ ነው ሕመምተኛነት?

ከተክለኃይማኖት አደባባይ የበላይ ተክሉን ብስኩት ቤት ይዘህ ቁልቁለቱን ወርደህ የሱማሌ ተራን ዳገት ወጥተህ ስትጨርስ የሚመጣው አደባባይ ላይ ፊትለፊት የሚታየው በተለምዶ የሰፈር በኒን መስጊድ ተብሎ የሚታወቀው መስጊድ ሲስራ፣ በፊታውራሪ ኃበተጊዮርጊስና በጣይቱ ምን ዓይነት መከራና እንግልት ሙስልሞች ላይ ሲደርስ እንደነበር የታሪክን መዝገብ ትንሽ ብታገላብጥ፣ ዛሬ አሁን እዚህ ለመፃፍ በተዳፈርከው ትንሽ ባፈርክ ነበር።

አየህ ዋጆ ሆረስ፣ የኢትዮጵያ ነገስታት ታሪክ፣ እኔና አንተን ብቻ ሳይሆን፣ የመላውን የሓገሪቱን የታሪክ ባለሙያዎች፣ልሒቃንና ምሕራኖችን ሁሉ ያላስማማና የምያነታርክ ጉዳይ ነው። ስለዚህ የምታመጣውን ተረት ተርት ሁሉ እኔ ዝም ብዬ አልጋተውም እሺ። ስትፈልግ አንተ ምኒልክም ይሁን መይሳው ካሳ፣ ጠቅልም ይሁን በዝብዝ ካሳን ማወደስ ብቻ ሳይሆን ማምለክም መብትሕ ነው፣ ብዙ ዓይነት የታሪክ ትርጓሜ ያለው ሕዝብ ፊት ግን ያንተን ውዳሴ ማንፀባረቅና አሜን ብላችሁ ተቀብሉ ማለት፣ ብልኃታችንን መሳደብ ነው።

ነገስታት ሁሉም በጊዜያቸው ጥሩም መጥፎም ሰርተው አልፈዋል። ጀግንንት ግርማና ሞገሳቸውን ብቻ ልትመግቡን ስትሞክሩ፣ የለም መጥፎ ስብዕናቸውና ወንጀሎቻቸውም አንድ ላይ ይዘከር ነው የምንለው፣ ምክንያቱም ታሪክ ታሪክ ነውና። ይህም በሽተኛነት ወይም ሕመምተኛነት ከሆነ፣ እንዳሻው ይሁን እንግዲህ።
እስቲ አንድ ቦታ ምኒልክ ሙስሊሞችን ሲያጠቃ በታሪክ ጥቀስ?
እሺ መልካም፣ እስቲ ታሪክን ከሶዶ ጉራጌ ሳጥን ወጣ ብለህ በሌላው በምትወደው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጫማ ላይ ቆመህ ደግሞ ቃኘውና እስቲ ምን ትላለህ።

Horus
Senior Member+
Posts: 40193
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አጼ ምኒልክ እና የኢትዮጵያ ሙስሊሞች (ባላገሩ ቲቪ)

Post by Horus » 28 May 2020, 03:37

አቶ አፕዲአራኤ ወይም ዎያኔ

ነገሩን ግል ጉዳይነት እናውጣው ። አንተ በትክክል ወያኔ ነህ ። ለምን በል? ዘመድችህ ሶዶች እያልክ ዋጆ ተለኛለው ! አየህ ዋጆ የክስታኔ አጠራር ይሁን አይሁን አታቅም። በማያገባህ ገብተህ ነው እንደ ባለጌ ቆማጣ ምትፈተፍት ። ጉራጌ 50% ሙስሊም ነው። አንተ እኔን ስለ ሙስሊም አትነግረኝም ። ጉራጌን በሃይማኖት የከፋፈለ የሱማሌው ግራኝ መሃምድ ነው። ያን አሁን እንተወው ።

እኔ የተማርኩት ናቲቪቲ ነው። በኒን መስጊድ እንደ መዳፌ አውቀዋለሁ ። የባኒያን ሰፈር ማለትም የሲክ ህንድ ነጋዴዎች ሰፈር መስጊድ ሲሰራ ምኒልክ አደረገ የምትለውን ግፍ ለምን በመረጃ አታሳይም?

ያንተ ቀን ያለፈበት አጉል ጸረ ምኒልክ ለቅሌት እንጅ አንተ በምኒልክ ሚዛን ምትለካ ሰው ልትሆን አትችልም ። ምኒልክ ከሙስሊም አረብ ባሪያ ሕንብ ሻጮች ተከላክሎ ነጻ ሰው ያደረገህ የኢትዮጵያ አባት ነው። ዛሬ አንተ በዚህ ማመን የለብህም !! ግን ታሪክን እንኳን አንተ እግዚአብሄር ራሱ ሊለውጠው አይችልም !!

በኒን ሰፈር ማለት የሙስሊም ሰፈር ማለት አይደለም !! የባኒያን ሰፈር ማለትም የህንዶች ሰፈር ፣ የመርካቶ ጨርቃጨርቅ ነጋዴ የሲክ ህንዶች ሰፈር ማለት ነው። ባኒያን ማለት ነጋዴ ማለት ነው ።

እጅህን ከታላቁ ምኒልክ ላይ አንሳ !!! ከማፈር ትድናለህ !!

EPRDF
Member
Posts: 2162
Joined: 26 Jan 2010, 12:58

Re: አጼ ምኒልክ እና የኢትዮጵያ ሙስሊሞች (ባላገሩ ቲቪ)

Post by EPRDF » 28 May 2020, 21:49

ዘመድችህ ሶዶች እያልክ ዋጆ ተለኛለው ፦ አየህ ዋጆ የክስታኔ አጠራር ይሁን አይሁን አታቅም።
ምነው ከፋህሳ ዋጆ ሆረስ ? ከወለኔ ቃል ተውሼ ላንተ ሶዶው ባሳቅፍህ ቅር ያሰኛል እንዴ ? ጉራጌ ሁሉም አንድ ነው ስትለን አልነበር እንዴ ?
ጉራጌ 50% ሙስሊም ነው።
እርግጠኛ ነህ ?
ጉራጌን በሃይማኖት የከፋፈለ የሱማሌው ግራኝ መሃምድ ነው።
በመጀመሪያ፣ ግራኝ መሃመድ የሚባል ሰው የለም። ግራኝ አህመድ ነው ትክክለኛ መጠሪያው። ቀጥሎም ግራኝ አህመድ ከሐረር የወጣ ኢትዮዽያዊ መሪ እንጂ አንተ ለመሳል እንደፈለግከው ሱማሌ አልነበረም። በመጨረሻም፣ ጉራጌም፣ እንደ ሓረር oral history የሀርላ ዘር የሐረሪ ብሔረስብ አባል ነው። ለጦርነት ከሐረር ሄዶ ሸዋ ውስጥ ተውጦ የቀረ የሐረሪ ብሔረሰብ አካል ነው። ያም ሶዶ ጉራጌንም ትግሬዎች ከሰሜን መጥተው ቁርባን ኣስውጠው ሳያስከረስኑት ያጠቃልላል።
በኒን ሰፈር ማለት የሙስሊም ሰፈር ማለት አይደለም ፦፦ የባኒያን ሰፈር ማለትም የህንዶች ሰፈር ፣ የመርካቶ ጨርቃጨርቅ ነምጋዴ የሲክ ህንዶች ሰፈር ማለት ነው። ባኒያን ማለት ነጋዴ ማለት ነው ።

ዋጆ ሆረስ ጤና የለህም እንዴ? እኔ በኒን ሰፈር ብዬ መስጊዱ ያለበትን ቦታ አመላከትኩህ እንጂ የሙስሊም ሰፈር ነው ብያለሁ እንዴ እስቲ ተረጋጋ!
ሲክ ደግሞ ህንድ ውስጥ ካሉ የኃይማኖት ዓይነቶች አንዱ ነው እንጂ የሕንድነት መገለጫ አይደለም። ባንያን ደግሞ በእንግሊዝኛ ነጋዴ የሚል ትርጉም ቢሰጥም፣ ወደ ሕንዶች ስንመጣ ግን፣ ባንያን ሕንድ ሐገር የሚገኝ የዛፍ ዓይነት ሲሆን ባኒያል ወይንም ቤንጋሊያን ሲል ደግሞ ከindian subcontinent አንዱ ከሆነው ቤንጋል ክፍለሐገር ከቃሉ የመነጨ ለሕንድነት መገለጫ የመጣ ቃል ይሆናል። ደስ እንዳለህ ተርጉመው ይህ አያጣላም፣ ዋናው ጉዳይ ግን እዛ ጋ ያለውን መስጊድና ታሪካዊ አመሰራረቱን ማወቅ ላይ ነው።
እጅህን ከታላቁ ምኒልክ ላይ አንሳ ፦፦፦ ከማፈር ትድናለህ ፦፦
አዪኢኢ ዋጆ Horus my royal azzkisser አንተም ኣላፈርክም!!

Horus
Senior Member+
Posts: 40193
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አጼ ምኒልክ እና የኢትዮጵያ ሙስሊሞች (ባላገሩ ቲቪ)

Post by Horus » 29 May 2020, 01:14

አንተ ቀባጣሪ ዲኑ የጠፋብህ ወያኔ፣
ይህ ሃረግ በምንም መልኩ ስለ ጉራጌ፣ ስለ ወለኔ አልነበረም፤ ስለ መጀመሪያ ያዲሳባ መስጊድና ምኒልክ ነበር ። ጉራጌ ሲተርት ነገር የባለቤቱ ነው ይላል። ይህ እንግዲህ ሾርባ ነው እንደ አፈላሀው አንተው ጠጣው። ልንገርህ ክስታኔ ጉራጌ ዬምጣቢ ይላል (እንኳን ደህና መጣህ ማለት ነው) ፤ ሰባት ቤት ጉራጌ የተምቢ፣ ዬተምቢ ይላል ። አንተ ደንቆሮ ሆነህ በማያገባህ ሌላ ብሄረሰብ ካልቸር ገብተህ ትፈተፍታለህ ። ደሞ ዋጆ በዋናነት የስልጤ አባባል እንጂ የወለኔ አይደለም ። አንተ ከዚህ ዉጣ፣ በቃ ክስታኔ ዋጆ አይልም ማለት አንድን ባህል በትክክል ማወቅና በስልጤ ጉራጌ ዋጆ ነው። ሰባት ቤት የተምቢ ትክክለኛው ነው ። በክስታኔ ዬምጣቢ ነው ማለት የህዝቦችን ትክክለኛ ባህል ማወቅ ነው። አንተ በማታቀው ገብተህ መርዝ ት ዘራለህ፤ ወዳቂ !! ራሱ በኒን መስጂድ ማለት ትርጉሙን አታቀውም ። ስለ ሲክ የቀባጠርከውም ስህተት ነው። ሲኪዝም ሃይማኖት ብቻ ሳይሆም ያንድ ቅኝ ገዝዎችህን ለመዋጋት ሆነ ብሎ የተፈጠረ እምነትና ጎሳ ነው ። ለምን አርፈህ ከመሰሎችህ ጋር አትነታረክም ?

Post Reply