Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Mahlana
Member
Posts: 1116
Joined: 25 Jan 2018, 08:33

Whoops!!!

Post by Mahlana » 25 Apr 2020, 09:15

Kind of..
"I am not satisfied with only the 600 square KMs of Gondars fertile land. Give me half of Gondar!"

ለህዳሴ ግድቡ የውኃ ሙሌት በዋሽንግተን የተደረገው ድርድር ጭብጦች ከግንዛቤ መግባት እንዳለባቸው ሱዳን አስታወቀች

22 April 2020

ዮሐንስ አንበርብር

የህዳሴ ግድቡ የውኃ ሙሌትን አስመልክቶ ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን በአሜሪካ ዋሽንግተን ከተማ ሲያደርጉት በነበረውና በተቋረጠው ድርድር ስምምነት የተደረሰባቸው ጭብጦች፣ ቀጣዩን ድርድርና የውኃ ሙሌት ለማከናወን ከግንዛቤ እንዲወሰድ ይገባል ስትል ሱዳን አስታወቀች።

የሱዳን መንግሥት ይኼንን ያስታወቀው ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ከግብፅ መንግሥት የግብርናና የውኃ ሀብት ሚኒስትሮችና ከግብፅ ብሔራዊ ደኅንነት ኃላፊ ጋር፣ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በካርቱም ያደረጉትን ውይይት ተከትሎ ባወጣው መግለጫ ነው።

የሁለቱ አገሮች ኃላፊዎች የተቋረጠውን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውኃ አሞላልና አለቃቀቅ በተመለከተና ድርድሩ በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ማድረጋቸውን የገለጸው መግለጫው፣ ከዚህ በተጨማሪም በሁለቱ አገሮች የሁለትዮሽ የትብብር ጉዳዮች ላይም መምከራቸውን አመልክቷል።

በውይይታቸው ወቅትም የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ የህዳሴ ግድቡ የውኃ ሙሌትን አስመልክቶ፣ በአሜሪካና የዓለም ባንክ ታዛቢነት በዋሽንግተን ሲደረግ በነበረው ድርድር ስምምነት የተደረሰባቸው ጭብጦች፣ በቀጣይ ለሚደረገው ተመሳሳይ ድርድርና የውኃ ሙሌቱን ለማከናወን ከግንዛቤ እንዲወሰድ መንግሥታቸው ፅኑ ፍላጎት ያለው መሆኑን አስረግጠው መናገራቸውን መግለጫው ያመለክታል።

ከዚህ በተጨማሪም እ.ኤ.አ. በ2015 በሦስቱ አገሮች መሪዎች የተፈረመው ህዳሴ ግድቡን የተመለከተው የመርህ መግለጫ ስምምነት ሱዳን አጥብቃ የምትገዛበት ስለመሆኑም ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ መግለጻቸውን የሱዳን መንግሥት በመግለጫው አስታውቋል።

የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስተር በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያና ግብፅ በመጓዝ የተቋረጠው ድርድር በሚጀምርበት ሁኔታ ላይ፣ ከሁለቱ አገሮች መሪዎች ጋር ለመምከር ፕሮግራም መያዛቸውንም መግለጫው ያመለክታል።

የአሜሪካ የገንዘብ ተቋም ኃላፊ ስቴፈን ምኑቺን ከሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ጋር የህዳሴ ግድቡ ድርድር በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ በስልክ መወያየታቸውን፣ ከሦስት ሳምንት በፊት መዘገባችን ይታወሳል።

ሁለቱ ወገኖች ባደረጉት በዚህ የስልክ ውይይትም የህዳሴ ግድቡን ድርድር በፍጥነት ማጠናቀቅ አስፈላጊነት ላይ መግባባታቸውን፣ የኮሮና ቫይረስ በዓለም አቀፍ ደረጃ እያደረሰ ያለውን ጉዳት መንግሥታት ተቆጣጥረው ቀልባቸውን ከሰበሰቡ በኋላ፣ ድርድሩን ከተቋረጠበት ማስቀጠል ተገቢ ስለመሆኑ ሐሳብ ተለዋውጠው ነበር።

ከዚህም በመቀጠል የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ ከሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር በስልክ መወያየታቸውን፣ አሜሪካ ሱዳንን ከአሸባሪነት ዝርዝር ውስጥ ለመሰረዝ በያዘችው ዕቅድ ላይ መምከራቸውን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ ያመለክታል።

ሱዳን የህዳሴ ግድቡን አስመልክቶ ለመያዝ የፈለገችውን ሚና አስመልክቶ የተጠየቁት የኢትዮጵያ የውኃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ስለሺ በቀለ (ዶ/ር)፣ ኢትዮጵያ የሱዳንን ፍላጎት በበጎ እንደምትመለከተው ገልጸዋል።

ሱዳን የታችኛው የዓባይ ተፋሰስ አካል እንደ መሆኗ የህዳሴ ግድቡ የውኃ ሙሌት ጉዳይ የሚመለከታት ስለሆነ፣ ድርደሩን ያስተጓጎሉ ምክንያቶች ተቀርፈው መፍትሔ ለማምጣት የምታደርገው እንቅስቃሴ እስከሆነ ድረስ የኢትዮጵያ መንግሥት በበጎ እንደሚመለከተው የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ኢትዮጵያ በሉዓላዊ ግዛቷ ውስጥ ስለምትገነባው ግድብ ለሌሎች አገሮች ጫና እንደማትንበረከክ፣ ነገር ግን የኢትዮጵያን ጥቅም በሚያስጠብቅ ትብብርን መሠረት ባደረገ መፍትሔ እንደምታምን አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያ በያዘችው አቋም መሠረት የግድቡ የውኃ ሙሌት በሚከናወንበት ወቅት ወደ ግድቡ የሚመጣው የውኃ መጠን 35 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብና በታች ከሆነ በድርቅ ወቅት አመላካች ተደርጎ እንዲቆጠር ኢትዮጵያ አቋሟን ስታስታውቅ፣ በአሜሪካ ሲደረግ በነበረው ድርድር ደግሞ የድርቅ ወቅት አመላካች 37 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ የሚል ሐሳብ ተንፀባርቆ ነበር።


https://www.ethiopianreporter.com/article/18668