Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 40115
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ግዴታ የፈጠራ እናት ናት፤ በልክ የተበላ መርዝ መግደል ሳይሆን ያጠነክራል !! የኮሮና ጥቅም !!!

Post by Horus » 30 Mar 2020, 02:23

ልብ በሉ ያድናል አላልኩም ። ኮሮና ቫይረስ በመሰረቱ መርዝ ነው ። ላንዳንዶች ገዳይ ነው፣ ለደካሞች ማለት ነው ። ላንዳንዶች ማጠንከሪያ መሳሪያ ነው ። ሌላው መርዝም፣ መድሃኒትም፣ እንዲሁ ነው ።

ሃሳብም፣ ተግባርም፣ ልማድ፣ እምነትም፣ ዘረኝነትም፣ ጎሰኝነትም፣ ዘፈንም፣ ዳንስም፣ ምግብም፣ ማርም፣ ሌላም ሌላም በልክ ያለመልማል፣ ሲበዛ ይገድላል !!!

ክሮኖና ከዚህ የተለየ ስራ የለውም ። ራሱን ሳያደራጅ ሲሰንፍ የነበረውን ባጭሩ ቀጥፎ ያሰናብታል ። የሚያስቡት፣ ለሆያ ሆዬ ሳይሆን ለሳይንስና እርግጠኛ እውቀት የሚተጉትን ይበልጥ አጠናክሮ፣ ይበልጥ እንዲያስቡ፣ እንዲፈለስፉ፣ እንዲመራመሩ ግዙፍ ገፊ፣ ገፍታሪ ሃይል እየሆነ ነው።

በዚህ በሽታ የሚያልቁ ደካሞች፣ ያልተዘጋጁ እልፍ ናቸው ።

ከዚህ በሽታ አገግመው እንደ ገና የሚነሱ እልፍ ናቸው።

ይህን በሽታ ተከላክለው የሚቋቋሙት ሃይለ ኢሙኒቲ የገነቡ መልካም የኑሮ ዘዴ የሚከተሉ እልፍ ናቸው ።

እንዲያውም ይህ በሽታ ያመጣውን እድልና አጋጣሚ በከፍተኛ ጥበብ በመቀበልና በመጠቀም አዲስ ነገር የሚሰሩ፣ የሚፈለስፉ፣ የሚያድጉ፣ የሚመነደጉ ጸረስብራቶች እልፍ ናቸው ።

ጸረስብራት እኔ ሆረስ የፈጠርኩት ቃል ነው። ጸረስብራት ማለት በአንድ ችግር፣ አደጋ፣ ቀውስ፣ ጥፋት የሚጎዳ፣ የሚጠቃ ሳይሆን በዚያ ጥፋት ምክንያት የሚማር፣ የሚያድግ፣ የሚገነታ፣ የሚበረታ ማለት ነው።

ኮሮና ቫይረስ፣ የዘር ፖለቲካ፣ የመንጋ ሳይኮሎጂ፣ እና መሰሎቹ ሁሉ ተፈጥሮዋቸው አንድ ነው ። ደካማውን ይገድላሉ፣ አዋቂውን ያገነታሉ !!!

ኬር ለኢትዮጵያ