Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Ejersa
Member
Posts: 3978
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

Shame on you!!!!

Post by Ejersa » 23 Mar 2020, 21:21

ስኳርና ኬሚካል ከቀይ አፈር ጋር በመቀላቀል ማር ነው ብሎ ለመሸጥ ሲያዘጋጅ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 14 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ስኳር እና ኬሚካል ከቀይ አፈር ጋር በመቀላቀል ማር ነው ብሎ ለመሸጥ ሲያዘጋጅ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ግለሰቡ ሙሉ መኖሪያ ግቢ ተከራይቶ ህገ - ወጥ ተግባሩን ሲፈፅም በቁጥጥር ስር ሊውል የቻለው ፖሊስ በጥርጣሬ ባደረገው ማጣራት ነው።

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘም አንድ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት ይገኛል።

ግለሰቡ መርካቶን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች ማር ነው ብሎ ያዘጋጀውን ባዕድ ነገር ሲሸጥ እንደቆየ ተገልጿል።

በተጨማሪም ከኮሮና ቫይረስ ወረርሸኝ ጋር ተያይዞ ተገቢ ያልሆነ ድርጊት በሚፈፅሙ እና ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ ቁጥጥሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም የክፍለ ከተማው የወረዳ 11 ንግድና ኢንዱስትሪ ፅህፈት ቤት ሃላፊ መናገራቸውን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)



Digital Weyane
Member+
Posts: 9835
Joined: 19 Jun 2019, 21:45

Re: Shame on you!!!!

Post by Digital Weyane » 23 Mar 2020, 23:45

ከሚኒሊክ ቤተ መንግስት በኢ-ዴሞክራስያዊ አገባብ ዱንጋይ ኡየወረወራችሁ ኡስከ መቀሌ ድረስ ባታባርሩን ኖሮ፡ ዛሬ ቀይ አፈርን ማር ነው ብለን አንሸጥላችሁም ነበር። ሼም ኦን ዩ!! :evil: :evil:

ዙፋኑ ዎደ ኡኛ እስኪመለስ ድረስ ትግላችን ይቀጥላል። ኡናሸንፋለን!!

Post Reply