Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Hameddibewoyane
Member
Posts: 3890
Joined: 25 Sep 2019, 02:42

የብሄር ፓለቲካ ጦስ!!!!

Post by Hameddibewoyane » 25 Feb 2020, 15:19

የብሄር ፓለቲካ ዞሮ ዞሮ አላማው ነፃነት ሳይሆን ዘረፍና አፈና ነው።ጥላቸውና ልዩነታቸውም የርእዮተ አለምና የመርህ ሳይሆሆን ቀጥሎ መዝረፍ ያለብኝ እኔ ነኝ አንተ አይደለህም የሚል ነው።ሀሉም ፓርቲዎች ደጋፊ መንጋ እንጂ የሚመሩበት አይዲዮሎጂ የላቸውም። ደጋፊዎዎቹም ፍላጎታቸው ነፃነት ሳይሆን እኛ የምንወደው ሰውዬ የሚመራው ፓርቲ ወይም የኛ ብሄር የተደራጀ ዘራፊ ስልጣን ይያዝ የሚል ነው።ትግሬ ህወሀት ይዝረፍ ሲል ፥አማራ ደግሞ አብን ይዝረፍ ባይ ነው።ኦሮሞ ደግሞ ገሚሱ ኦፌኮ ይዝረፍ ሲል፤ ገሚሱ ደሞ ኦነግ ብዙ አመት ስለታገለና ብዙ አመት ጫካ ሆኖ ዘሪፊና ጨቋኞችን ስለታገለ ካሳ እንዲሆነው ኦነግ ይዝረፍ ይላል።የጅማና አከባቢው ስው ደግሞ አብይ የኛ ሰው ስለሆነ ብልጥግና ነው መዝረፍ ያለበት ባይ ነው።

የሆነው ሆኖ ሁሉም ፓርቲዎች የስም እንጂ የአላማ ልዩነት የላቸውም።ቀጥሎ ሰላማዊና ተአማኒ ምርጫ ቢደረግ እንኳን የሚያሸንፈው ብዙ ጭፍን ደጋፊ ያለው ማጅራት መቺ ቡድን እንጂ ።የነጠረ የፓለቲካ የአይዲዮሎጂ ያለው ቡድን ወይ ፓርቲ አይደለም።

ሲጀመር አይደለም ትክክለኛ የተሳሳተ አይዲዮሎጂ ያለው ፓርቲ ራሱ መኖሩን እንጂ።ለዛ ነው ፍክክሩ በደጋፊዎች ተወዳጅ መሆን ላይ እንጂ ሀሳብ ላይ የተመሰረተ ያልሆነው።ውድድሩ የተመሰረተው የአስተሳሰብ ላይ ሳይሆን በብዙ መንጋ ተወዳጅ መሆን ላይ ነው። በመንጋ ብዛት ስልጣን የሚይዝ ቡድን ደግሞ የሚመራው በሪዝንና በአስተሳሰብ
ሳይሆን በመንጋው ፍላጎትና ምኞት ነው።

በአስተሳሰብ እንጂ በመንጋ ድጋፍና ምኞት በመመራት ደግሞ ሀገር ትፈርሳለች እንጂ አትበለፅግም።ብጥብጥ እና ሁከት እንጂ ሰላም አይሰፍንም።ርሀብ ፤ድንቁርና፤ሙስናና ጭቆና ይፍፍማል እንጂ አርነትና የኢኮኖሚ እድገት ከመጣ ከምላሴ ፀጉር ይነቀል