Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Hameddibewoyane
Member
Posts: 3890
Joined: 25 Sep 2019, 02:42

መደመር ማለት ለህወሓት ፖለቲካዊ አጀንዳ ማሳጣት ማለት ነው!!!

Post by Hameddibewoyane » 25 Feb 2020, 14:39

እነሆ ዶ/ር አብይ፣ ህወሓት እንዴት መታገል እንዳለበት ያወቀው በጥዋቱ ነው፣ ህወሓት ከጭቁኑ የትግራይ ህዝብ ድጋፍ ለማግኘት፣ የትግራይ ተወላጆች በዘራቸው ምክንያት እየታሰሩ ነው፣ ዶ/ር አብይ የትግራይ ጠላት ነው በማለት፣ ጊዜያዊ የፖለቲካ ትርፍ አግኝታለች። ዛሬ በትግራይ ተወላጁ ዶ/ር አብርሃም የሚመራ የትግራይ የብልፅግና ፓርቲ አመራር፣ የታሰሩት የትግራይ ተወላጆች ፌደራል መንግስት ምህረት እንዲያደርግላቸው ባቀረበው ጥሪ መሰረት፣ ታስረው የነበሩ የትግራይ ተወላጆች እንደሚፈቱ ፌደራል መንግስት አስታውቀዋል።

የትግራይ ተወላጆች መፈታት ለህወሓት ሰርግ ሳይሆን መርዶ ነው፣ አምባገነኑ የህወሓት አመራር የውስጡን ፖለቲካዊ ኪሳራ ከማየት የውጩን በማየት እና በማጋነን ካሁን ቦሃላ ጩቁኑን የትግራይ ህዝብ እየዋሸ የሚኖርበት ጊዜ አብቅተዋል። ተከበናል ተወረናል የሚሉ አማርኛዎች ቦታ የላቸውም።አሁን ብልፅግና ፓርቲ በትግራይ የሚገኙ የፌደራል መንግስት መዋቅሮችን በመጠቀም፣ የትግራይ ህዝብ ሌላ አማራጭ እንዳለው ማስረዳት እና ማስተማር አለበት፣ ለምሳሌ ብልፅግና ፓርቲ በመቀሌ የሚገኙ የፌደራል መንግስት መገናኛ ቡዙሃን እንደነ ፋና ሬድዮ እና ቲቪ መቆጣጠር አለበት፣ በህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ የተያዙ የፌደራል መስርያቤቶች፣ ብልፅግና ፓርቲ ለአዳዲስ የፓርቲያቸው አባላት ማስረከብ አለበት። የመከላከያ እና የደህንነቱ ሃይል ተጠቅሞ የብልፅግና ዓረና አባላት ጥበቃ ማድረግ አለበት!

አሁን የህወሓት አጀንዳ ምን ሊሆን ይችላል? የተፈቱ ተጋሩ ወንድሞቻችን፣ በሌላ አገር መንግስት የተፈቱ እስኪመስሉ ድረስ ትግራይ ሲሄዱ ደማቅ አቀባበል ልታደርግ ነው፣ ህዝቡን ለመደለል በዘራቸው ምክንያት ታስረው የነበሩ ተጋሩ ወደ አገራቸው(በህወሓት አባባል ትግራይ) ገብተዋል ህዝቤ ሆይ ውጣ እና የህወሓት ባንዴራ ይዘህ ተቀበል ልትል ነው፣ ይሁን ይህም ለሳምንት ብቻ ነው። ህወሓት ግን በመደመር ስሌት አጀንዳ እያጣች ነው፣ ህወሓት አጀንዳ በማሳጣት፣ የታሰሩት ተጋሩ ቃሊት ደረስ ሄዳቹ በማየት ህወሓትን አጀንዳ ያሳጥችዋት፣ የዓረና የታንድ እና ብልፅግና ከፍተኛ አመራሮች ልትመሰገኑ ይገባል። ትግራይ ውስጥ ታስረው የሚገኙ የዓረና አባላት እስኪፈቱ ድረስ እና ትግራይ ለሁሉም ተጋሩዎች እኩል እስክት ሆን ድረስ ትግላችን ይቀጥላል፣ ድል ለትግራይ ህዝብ ሞት ለህወሓት አመራሮች።