Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abaymado
Member
Posts: 4592
Joined: 27 Sep 2017, 21:56

አብን እያንሰራራ ነው ! አሁን ትልቁ ቁም ነገር አብን ትላልቅ የበሰሉ አማራዎችን ማሰባሰብ አለበት: ለምሳሌ ታስረው የነበሩትን ጀነራሎች: ዩሐስን ቧ ያለው ...

Post by Abaymado » 24 Feb 2020, 04:45


አብን እኮ ከሞተ እኮ ቆየ: በስንት መከራ ነው ብቅ እያለ የነበረው:: አመራሩ ደካማ ከመሆኑ የተነሳ አዲስ ሕሳብን እና ስትራተጂን ነድፎ መቀጠል አልቻለም:: አብን የበሰለ መሪ ነው የሚያስፈልገው::
አብን የህዝቡን ፍላጎትና ድምፅ ማዳመጥ አለበት:: በለጠ ሞላን እንደ ሊቀመንበር አልቃወውምም ግን ትንሽ ቀዝቀዝ ያለ ይመስለኛል:: ይልቅ ዩሱፍ ኢብራሂም ቦታውን ቢይዘው ጥሩ ነበር ብዬ አምናለሁ: ደፋር ነው:: አሁንም ቢሆን ምክትል ስለሆነ ይናበባሉ የሚል ግምት አለ::

ሰሞኑን ሲናፈስ የነበረው: ጋሻው መርሻን ከፓርቲው ያባርራል የሚል ነበር : ግን አሁን እንዳየነው የህነ ቦታ ላይ ስልጣን አግኝቷል:: ጋሻው የሚባል ሰው የሚለቀው መረጃ አይመቸኝም:: ምናልባትም ከፋፋይ ነው::
ማባረሩ ግን ተገቢ አይመስለኝም:: ፓርቲው አባሮ አይችለውም::

አሁን ትልቁ ቁም ነገር አብን ትላልቅ የበሰሉ አማራዎችን ማሰባሰብ አለበት:: ለምሳሌ ታስረው የነበሩትን ጀነራሎች: ዩሐስን ቧ ያለው ...
እንዲሁም በአዲስ አበባ: በገጠሪቱ አማራ ክልል ብዙ እንቅስቃሴ ስለሌለ ሊታሰብበት ይገባል:: ከአማራ ክልልም ሊታሰብበት ይገባል::