ትላንት ጥቂት ጓደኞቼ ወደ አገር ለመሄድ የመግቢያ ቪዛ ለማስመታት ምን ምን እንደ ሚያስፈልግ ለመጠየቅ ስልክ ደወሉ ። አንዲት ሴት ስልኩን መለሰች ። ምን ምን ይዘን እንምጣ ብለን ጠየቋት ። እሷም ፓስፖርትና 70 ዶላር ብቻ ነው የሚያስፈልጋችሁ አለቻቸው ። ደግመው ከሩቅ ቦታ ስለሆነ የምንመጣው ባክሽን አስፈላጊው ነገር ሁሉ ንገሪን አሉዋት ። እሷም ደግማ ሌላ ምንም አትፈልጉም አለች ። ያ የሆነው ትላንት ነበር።
ዛሬ ቆንስላው ላይ 11፡00 ዐM ላይ ደረሱ ። የጉዳያቸው ሂደት ለመጀመር የሚሞላ ፎርም ሲጠይቁ ፎርም ስላለቀብን አባዝቼ ልምጣ ብላ ሄደች ። ሄዳ ድፍን 45 ደቂቃ ቆይታ ፎርም ይዛ መጣች ። ፎርም ሞልተው ከ70 ዶላር ጋር ሰጡዋት፤ ይህ የሆነው 12፡30 ላይ ነበር ።
ነገር ግን ሰራተኛዋ ቀላ ያለች ረጅም ጸጉር ያላት ፤ አይ ዶላሩ በመኒ ኦርደር መሆን አለበት ፤ ደግማም አንድ ጉርድ ፎቶ ያስፈልጋቿል አለች። ይህ ሲሆን በጥም ደንግጠው መነው ትላንት ደውለን ስንጠይቅሽ ስለ ፍቶም ሆነ መኒ ኦርደር ሳይሆን 70 ዶላርና ፓስፖርት ብቻ ነው ምትፈልጉት አላልሽም ወይ አሏት ። እሷም እኔ አይደለሁም ብላ ካደች ። እነሱ ግን ድምጿን በትክክል የሷ እንደ አውቀውታል ።
አሁን በጣም ተረብሸው ፣ ከተማውንም ስለማናውቅ አሺ አሁን ከየት ነው ፎቶ ቤትና የመኒ ኦርደር ቦታ የምናገኘው ብለው ሲጠይቋት አንዲት አጠር ቀጠን ያለች ወጣት ሴት እዚያ ከመስተዋቱ ጀርባ ከሰራተኞቹ ጋር የተቀመጠች እኔ እዚያ ማዶ የራሴ ሱቅ አለኝ ብላ ይዛቸው ሄደች ። እሷም በነፍስ ወከፍ $20 ዶላር ላንድ ፎቶ እና $5 ዶላር ለመኒ ኦርደር አስከፈለቻቸው ።
ጉዳያቸው ጨርሰው ስንወጡ 1፡ 20 ማለትም 2 ሰአት ከ20 ነበር ግን በቆንስላው ውስጥ የነበሩት ሌሎች ባለጉዳዮች 2 ብቻ ነበሩ።
የደረሰባቸውን አሳፋሪ መጉላልትና ሌብነት ለሰዎች ሲነግሩ ይህ የሙስና ሲስተም ለረጅም ጊዜ የሚሰሩበት እንደ ሆነ ሌሎች ተመሳሳይ ነገር እንደ ደረሰባቸ አረጋገጡ።
የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባስቸኳይ እነዚህን ሌቦች አባርሮ ብቁና ታማኝ ሰዎች እንዲቀጥር ። ይህ በቀን ጅቦቹ ዘመን ያስመረረን ሌብነትና መጉላላት ይቁም ።
Re: በሎስ አንጀለስ የኢትዮጵያ ቆንስላ ውስጥ የሚካሄድ እጅግ አሳፋሪ ሌብነትና ብልግና
እንደዚህ ያሉ የድሮውን ደጋፊ ያሁኑን አደናቃፊ ተቀጣሪዎች መንግስትን አስጠልተው የዳያስፖራ ድጋፍ የሚያሳጡ ። እነሱን ማስወገድ ለፕሮስፐሪት ድጋፍ እንደ ማለት ነው !1