Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
free-tembien
Member
Posts: 1702
Joined: 02 Jul 2015, 20:56

FakeNewsAlert: Gonder Azezo fake muslim attack

Post by free-tembien » 02 Feb 2020, 16:38

Please wait, video is loading...

free-tembien
Member
Posts: 1702
Joined: 02 Jul 2015, 20:56

Re: FakeNewsAlert: Gonder Azezo fake muslim attack

Post by free-tembien » 02 Feb 2020, 16:40

#ብርቱ_መረጃ: የጥላቻ ሀሰተኛ መረጃዎችን እንከላከል‼
=====================================
* ጎንደር ሰላም ነው‼
ከሁለት ቀናት በፊት "#ጎንደር_አዘዞ ላይ ሙስሊሞችን ያነጣጠረ ጥቃት ተፈሟል" የሚል የተለያዩ የሀሰት ምስል መረጃዎችን በማስደገፍ የሀሰት መረጃ እየተሰራጨ ተመልክቻለሁ። የጉዳዩን አሳሳቢነት በመረዳት ቀኑን ሙሉ መረጃውን ለማጣራት ሞክሬያለሁ። እስካሁን ባለኝ መረጃ ያገኘሁት ፍንጭ የተሰራጨው የጥላቻ የሀሰት መረጃ መሆኑን ብቻ ነው።

በቦታው ካሉ ወገኖች እንደጠቆሙኝ ከሆነ ባሳለፍነው ህዳር ወር አዘዞ በሚገኝ የገበያ ቦታ እንደ ማንኛውም የእሳት አደጋ ተነስቶ ነበር። በወቅቱ በተነሳው ድንገተኛ የእሳት አደጋው ወፍጮ እና ሱቆችን የጎዳ ሲሆን ህዝቡ ተረባርቦ እሳቱን እንዳጠፋው ተረድቻለሁ።

በዚህ አጋጣሚ በሰላም ፣ በፍቅርና በህብረት ተከባብሮ በሚኖረው ኢትዮጵያዊ መካከል የሐይማኖት ግጭት ለመፍጠር የታሰበ መረጃ በመሰራጨቱ በእጅጉ አዝኛለሁ :( በህዝብ መጋጨትና በሀገር መታዎክ ከቶ ተጠቃሚው ማን ይሆን ?

ወገኖቸ ችግሮች ካሉ በመረጃና ማስረጃ አስደግፎ በኃላፊነት የማቅረብ የመረጃ ቅብብል ተገቢ የመሆኑን ያህል በሀሰት የሚሰራጩ መረጃዎችን አስነዋሪነት በማጋለጥ ልንከላከላቸው ይገባል። በዚህ አጋጣሚ በጎንደር አዘዞ ተነሳ ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ፍጹም የሀሰት መረጃ መሆኑን ላረጋግጥላችሁ እዎዳለሁ ። ወገኖቸ በመጨረሻም የጥላቻ ሀሰተኛ መረጃዎችን እንከላከል እላለሁ !

ቸር ያሰማን

ነቢዩ ሲራክ
ጥር 23 ቀን 2012 ዓም

Post Reply